Blog

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ የሚውል የሁለት ቢሊዮን ብር ፈንድ አፀደቀ፡፡ –

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ባደረገው ስብሰባ ለወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ለመመደብ የቀረበ ረቂቅ ሰነድ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

በዚህም መሠረት ዝርዝር ዕቅዶችን በማዘጋጀት እና በአፋጣኝ ከወጣቱ ጋር ሰፊ የምክክር መድረኮችን በማዘጋጀት የጋራ መግባባት ላይ ከተደረሰ በኃላ ወጣቶቹ በተለያየ ዘርፍ ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በከተማዋ ከ700ሺ በላይ ስራ አጥ ወጣት እንዳሉ መረጃዎች የሚያመለክቱ ሲሆን ይህ የሁለት ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ይህንን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ እና የከተማዋን ኢኮኖሚ በማነቃቃቱ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንደሚኖረውም ይጠበቃል፡፡

Copyright@2018 Addis Ababa City Resilience Project Office | All Rights Reserved